
ጸሎተ ቅዳሴ

ጸሎተ ቅዳሴ ምንድነው?
ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን ቃል ስንመለከት "ሥርዓት" ማለት አሠራር፣ አፈፃጸም ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን "ቅዳሴ" ደግሞ ምሥጋና ማለት ነው፤ ይኸውም ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምሥጋና ማለታችን ነው። እንግዲህ ቅዳሴ በሐዲስ ኪዳን የተጀመረው በቤተ ልሔም ሲሆን የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም በ፭ሺ ፭መቶ ዘመን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለው አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ ሰማያውያን መላእክት እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ምዕ. ፪ ቁ፥፲፬ ተጽፎ እናገኛለን።
ተጭማሪ መረጃለተጨማሪ መረጃ በዚህ እማኢል ያግኙን፡ secretary@st-teklehaimanotantwerp.org